ዘንድሮ የ42 መንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ ይጠናቀቃል

Published: Thursday, 03 October 2013 Written by Addis Zemen, Monday 30 Sept 2013, Page 02

የኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ዘንድሮ ከ28 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ 42 የመንገድ ፕሮጀክቶች ግንባታ ለማጠናቀቅ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ።

ባለሥልጣኑ እንዳስታወቀው፤ ከመንገድ ፕሮጀክቶቹ መካከል 73 በመቶ የሚሆኑት በአስፋልት ደረጃ፣ ቀሪዎቹ ከ26 በመቶ በላይ ደግሞ ደረጃውን በጠበቀ የጠጠር መንገድ የሚገነቡ ናቸው።
ከሚጠናቀቁት የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል የአዲስ አበባ
-አዳማ፣ ውቅሮ-ዓዲ ግራት- ዛላምበሳ፣ ጌዴኦ-ባኮ-ነቀምቴ፣ ጅማ-ቦንጋ-ሚዛን መንገዶች ይገኙባቸዋል።

እንዲሁም ኢሚ-ላብ-ጎዴ፣ አጉላዕ-በራህሌ-ዳሎል፣ ያቤሎ-ሜታ ገፈርሳ-ኦብሎ፣ አፖስቶ-ኢርባ ሞዳ-ዋደራ እና ዲዲግሳላ-ያሎ-ጨርጨር-መኾኒ ከሚጠናቀቁት መንገዶች መካከል መሆናቸውን ባለሥልጣኑ አስታውቀዋል።
ቀደም ባሉ ዓመታት የተጀመሩት እነዚሁ የመንገድ ፕሮጀክቶች አጠቃላይ ርዝመት ወደ ሦስት ሺ ኪሎ ሜትር እንደሚጠጋ ባለሥልጣኑ አመልክቷል።
ለፕሮጀክቱ ሥራ ማስፈፀሚያ የሚውለው አብዛኛው በጀት በኢትዮጵያ መንግሥት ሲሸፈን ቀሪው በብድር እንደሚሸፈን አስረድቷል።|
2006
 .ም ከሚጠናቀቁ የመንገድ ፕሮጀክቶች መካከል
 32ቱ በሀገር በቀል ተቋራጮች የሚሰሩ ሲሆን ቀሪዎቹ በውጭ አገራት የሥራ ተቋራጮች የሚሠሩ ናቸው።
የፕሮጀክቶቹ መጠናቀቅ ኢትዮጵያን ከጎረቤት አገሮች ጋር ፈጣን የንግድና የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት እንዲኖር የሚያስችል ነው።
በበጀት ዓመቱ ለሚከናወኑ የግንባታና ተዛማጅ ተግባራት ማስፈጸሚያ ከ
29
 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት መመደቡን ባለሥልጣኑ አስታውቋል።

 

This news is published on Addis Zemen, Monday 30 Sept 2013, Page 02

Hits: 1535