የአዲስ አበባ አስተዳደር የመሬት ኃላፊዎች ለልማት በሚቀርብ መሬት ላይ ለመወሰን አዳማ ከተዋል

Published: Tuesday, 04 November 2014 Written by Reporter Sunday 02 November 2014 Page: 03

የአዲስ አበባ   አስተዳደር  የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮና   የክፍላተ ከተሞች  ጽሕፈት ቤት ኃላፊዎች  2006 .. የሥራ አፈጻጸምና  ፣ 2007 በጀት ዓመት ዕቅድ  ላይ ለመነጋገር   አዳማ ከትመዋል፡፡

___________________

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 2038.5 ሔክታር መሬት ለተለያዩ ግንባታዎች ያቀረበው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በዚህ የበጀት ዓመት ከሁለት ሺሕ ሔክታር በላይ መሬት ለአልሚዎች ለማቅረብ ዕቅድ አውጥቷል፡፡ 

በ2006 ዓ.ም. ቢሮው ለልማት አቀርባለሁ ካለው መሬት፣ ብልጫ መሬት በማቅረብ የዕቅዱን 123 በመቶ ማሳካቱን ገልጿል፡፡ 

አስተዳደሩ 194.24 ሔክታር መሬት ለባለሀብቶች በሊዝ ለማስተላለፍ ዕቅድ ይዞ ነበር፡፡ ነገር ግን 258.95 ሔክታር መሬት በሊዝ ለአልሚዎች አቅርቧል፡፡ 

ለከፍተኛና ለመካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች 364 ሔክታር፣ ለመንገድና ወሰን ማስከበር 105 ሔክታር፣  ለጥቃቅንና አነስተኛ 86 ሔክታር፣ ለመኖሪያ ቤት ፕሮግራሞች 762 ሔክታር፣ ለልማት ተነሺዎች 87 ሔክታር፣ ቦታ መስጠቱን ለግምገማው በቀረበው ሪፖርት ተገልጿል፡፡

ለሌሎች ልማቶችም እንዲሁ ሰፋፊ ቦታ ማቅረቡ የተጠቀሰ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 2038.5 ሔክታር መሬት ለልማት መዋሉ ተጠቅሷል፡፡ 

በተለይ ቦሌና አቃቂ ቃሊቲ ክፍላተ ከተሞች ሰፋፊ የማስፋፊያ መሬት እንዳላቸውና በመሬት አቅርቦት በኩል የአንበሳው ድርሻ እንደሚይዙ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡ 

ቦሌ ክፍለ ከተማ ባለፈው ዓመት 600 ሔክታር መሬት አቅርቧል፡፡ ባልፀደቀው ዕቅድ ላይም በ2007 ዓ.ም. 760 ሔክታር መሬት ለተለያዩ ልማቶች ለማቅረብ አቅዷል፡፡ 

የአስተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎች በ2006 ዓ.ም. የሥራ አፈጻጸም ከተወያዩ በኋላ የ2007 በጀት ዓመት ዕቅድን ያፀድቃሉ ተብሏል፡፡ ኃላፊዎች ለዚህ ውይይትና የአቅም ግንባታ ሥልጠና ለመውሰድ አዳማ ከተማ ገብተዋል፡፡ 

አስተዳደሩ ሰፋፊ ቦታዎችን በተከታታይ በሊዝ ሽያጭ በማቅረብ የመሬት ዋጋ ንረት እንዲወርድ የማድረግ ዕቅድ እንዳለው ተገልጿል፡፡  

 

This content is published on, Reporter Sunday 02 November 2014 Page:  03

 

 

Hits: 690